Sunday, 03 September 2023 21:28

አያቴል ሞባይል “ኤስ 23+” የተሰኘ አዲስ ሞዴል ሞባይሉን በኢትዮጵያ አስመረቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ላለፉት አመታት በአገልግሎት ጥራታቸውና በዋጋቸው ተመራጭ የሆኑ የስልክ ምርቶችን ለአገራችን ገበያ ሲያቀርብ የቆየው አያቴል ሞባይል ቴክኖሎጂና ዲዛይን ኩባንያ፤ በአዳዲስ ፈጠራዎች የተሰራውንና ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ደረጃ የሚያሳዩ ኤስ 23+ የተሰኘ አዲስ ሞባይልን በኢትዮጵያ አስመረቀ፡፡
በአገራችን ገበያ በትራንሽን ማኑፋክቸሪንግ ኩባንያ ስር በመስራት አያቴል ብራንድ ስልኮቹን ለአገራችን ገበያ በማቅረብ ላይ የሚገኘው አያቴል ሞባይል ኩባንያ የተለያዩ ሞዴል ስልኮችን በማምረት ለአገራችን ገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡
የዘመኑ የካሜራ ቴክኖሎጂ የተገጠመለትና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚደገፍ ነው የተባለው አዲሱ አያቴል 23+ ሞዴል ስልክ የፊት ለፊቱ 32 ሜጋ ፒክስልና ዋናው ኋላ ካሜራ 50 ሜጋ ፒክስል የያዘና ጥራት ያላቸውን ምስሎች በዝቅተኛ ብርሃን ውስጥም ሆነ በርቀት  ለማንሳት አቅምና ብቃት ያለው መሆኑ በምርቃት ፕሮግረሙ ላይ ተገልጿል፡፡
የአያቴል ሞባይል ኢትዮጵያ ብራንድ ኃላፊ ሚስተር ኤሞን ጃ በዚሁ የምርቃ ፕሮግራም ላይ እንደተናገሩት ለኩባንያው አዲስ የሆነውን 23+ ሞዴል ስልክ በአለም ገበያ ከመቅረቡ በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ለማስመረቅ መምረጡ ኩባንያው ለኢትዮጵያና ለዜጎቿ የሚሰጠውን ከፍ ያለ ግምት ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
16 ጂቢ ራምና 256 ጂቢ ሜሞሪ የተገጠመለት አዲሱ አያቴል ኤስ 23+ በአንድ ጊዜ ብዙ ስራዎችን ለመስራት የሚስችልና ከፍ ያሉ የግራፊክስ ስራዎችን የመስራት የሚስችል አቅም ያለው እንደሆነም ነው በምርቃት ፕሮግረሙ ላይ የተገለፀው አያቴል በአለም አቀፍ ደረጃ ከ50 በላይ በሚሆኑ አዳዲስ ገበያዎች ውስጥ የሚንቀሳቀስ አለም አቀፍ ብራንድ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡



Read 712 times